Addis Ababa

Addis Ababa a song by Fikreaddis Nekatibeb on Foxsoundi — Free Music, Smart Streaming for Everyone

Addis Ababa by Fikreaddis Nekatibeb

Addis Ababa Lyrics

ሳናዎጋ ነጋ ነጋ ነጋ
ሃገሬ ወይና ደጋ: ወይና ደጋ
ሳናዎጋ: ነጋ ነጋ ነጋ
ሃገሬ ወይና ደጋ: ወይና ደጋ
ወይና ደጋ: ወይና ደጋ: ሳላዎጋ ነጋ
ወይና ደጋ: ወይና ደጋ: ሳላዎጋ ነጋ
እያለ ነጋ: እያለ ነጋ
ሆሆሆሆ ሃገሬ ወይና ደጋ
እያለ ነጋ: እያለ ነጋ
ዬዬዬሄሄሄ ሃገሬ ወይና ደጋ

አዲስ አበባ ላይ (የኔ የኔ) ተነገረ አዋጅ (የኔ የኔ)
ላንተ መሳይ ቆንጆ (የኔ የኔ) ላኔ መሳይ ልጅ (የኔ የኔ)
ሰረገላ እንዲጫን (የኔ የኔ) ሰልፍ እንዲዘጋጅ (የኔ የኔ)
እንዲተከል ድንኳን (የኔ የኔ) ለእንግዳ ወዳጅ (የኔ የኔ)

ግብር አስርቶ: ይጠብቃል እንጅ
ቃል አያጓድልም: ያአዲሳባ ልጅ
የሸገር አይናማ: አንተ የኔ ተቀባይ
በል ጠብቀኝ እንጅ: ጃንሜዳ አደባባይ

ኮኮብህ ኮኮቤ: የገጠመ ለታ: የገጠመ ለታ
ውድህና ውዴ: የገጠመ ለታ: የገጠመ ለታ
ለማሪያም መቀነት: ለገብርዔል ኩታ
ይህንን አድርጌ: እኔ ወዳጅህ
የምነግርህ አለኝ: የማጫውትህ
አጫውትሃለሁ: ወግ አሰባስቤ
ቁመቴም እንኳን ቢያጥር: ረዥም ነው ልቤ
ቁመቴም እንኳን ቢያጥር: ረዥም ነው ልቤ

አሆ ኦሆ የኔ አለም (የኔ የኔ)
አሆ ኦሆ የኔ አለም (የኔ የኔ)
አሆ ኦሆ የኔ አለም (የኔ የኔ)

ከዘር ከሃይማኖት (የኔ የኔ) ከቋንቋም ከነገድ (የኔ የኔ)
ሸገር ላይ ይተማል (የኔ የኔ) በአራት መንታ መንገድ (የኔ የኔ)
አቤት አፈጣጠን (የኔ የኔ) አዲስ ሰው ለማልመድ (የኔ የኔ)
ከዚህ ይመነጫል (የኔ የኔ) የኔና አንተ መውደድ (የኔ የኔ)

በአራቱም ማዕዘን: አውጥቶ እያገባ
ስንቱን አዋደደ: ወይ አዲስ አበባ
እንያያዝና: በል እንዘናከት
የፍቅር አባዜ: ወይ አለመታከት

ኮኮብህ ኮኮቤ: የገጠመ ለታ: የገጠመ ለታ
ውድህና ውዴ: የገጠመ ለታ: የገጠመ ለታ
ለማሪያም መቀነት: ለገብርዔል ኩታ
ይህንን አድርጌ: እኔ ወዳጅህ
የምነግርህ አለኝ: የማጫውትህ
አጫውትሃለሁ: ወግ አሰባስቤ
ቁመቴም እንኳን ቢያጥር: ረዥም ነው ልቤ
ቁመቴም እንኳን ቢያጥር: ረዥም ነው ልቤ
አሆ ኦሆ የኔ አለም (የኔ የኔ)
አሆ ኦሆ የኔ አለም (የኔ የኔ)
አሆ ኦሆ የኔ አለም (የኔ የኔ)
አሆ ኦሆ የኔ አለም (የኔ የኔ)
አሆ ኦሆ የኔ አለም (የኔ የኔ)
አሆ ኦሆ የኔ አለም (የኔ የኔ)
አሆ ኦሆ ናናሃሃሃ የአዲሳባው
አጫውትሃለሁ: አጫውትሃለሁ: ወግ አሰባስቤ
ቁመቴም እንኳን ቢያጥር: ረዥም ነው ልቤ
ቁመቴም እንኳን ቢያጥር: ረዥም ነው ልቤ
አጫውትሃለሁ: አጫውትሃለሁ: ወግ አሰባስቤ
ቁመቴም እንኳን ቢያጥር: ረዥም ነው ልቤ
ቁመቴም እንኳን ቢያጥር: ረዥም ነው ልቤ
አሆ ኦሆ ናናሃሃሃ የአዲሳባ

From the album: Misikir