Ybelegne

Ybelegne a song by Fikreaddis Nekatibeb on Foxsoundi — Free Music, Smart Streaming for Everyone

Ybelegne by Fikreaddis Nekatibeb

Ybelegne Lyrics

ይበለው ምናለ ልቤ ላንተ ፍቅር ከወደቀልህ
መቁረጡ ተስኖኝ ሁሌ የኔ ድካም ዘና ካረገህ
ይበለኝ ምናለ
ልቤ ወዶ ገብቶ መውጫው ከጠፋበት
እኔንም አጉላላኝ
እዳውን በራሱ መያዝ ሳይሆንለት
ይበለኝ
ወድጄ አንዴ ገብቻለው አላንገራግርም
በራሴ ልፍረደው ሌላ አላማርርም
ይበለኝ
ዘወትር ሳስብህ ልቤ ሲብሰለሰል
ማፍቀሬ እነደ ዝና አኮራብኝ መሰል
ሞኝ ናት ተላላ ብለህ አትማኝ
ጀግንነት አይደልም ስለበደልከኝ
ልቤ ባነገስክ ተፈቃሪ አድርጎህ
ጀግንነት ተሰማህ ልቤን አቁስለህ
•••
ጀግንነት ተሰማህ
ልቤን አቁስለህ
ጀግንነት ተሰማህ
ልቤን አቁስለህ
•••
ይበለው ምናለ ልቤ ላንተ ፍቅር ከወደቀልህ
መቁረጡ ተስኖኝ ሁሌ የኔ ድካም ዘና ካረገህ
ይበለኝ ምናለ
ልቤ ወዶ ገብቶ መውጫው ከጠፋበት
እኔንም አጉላላኝ እዳውን በራሱ መያዝ ሳይሆንለት
ይበለኝ
ይበለኝ ፍቅር እንጂ ወትሮም በቁሜ የወረሰኝ
መቁረጤም አይቀርም አንድ ቀን ሲለቀኝ
ይበለኝ
ችላ ብለኧኛል አይተህ መረታቴን
እኔ መቼም አልተው
ሠርክ አንተን ማለቴን
ያልደረሰበት ሰው ግልግል አያውቅም
ላፍታ እንደኔ ሆነህ ባየኧው ሁሉንም
የተራበ ልቤን ልብህ እየቀጣው
ላፍቅርህ አለ እንጂ ሌላ ምን ቃል ወጣው
•••
ጀግንነት ተሰማህ
ልቤን አቁስለህ
ጀግንነት ተሰማህ
ልቤን አቁስለህ
•••
ይበለኝ ይበለኝ ይበለኝ ይበለኝ
ይበለኝ ይበለኝ ይበለኝ ይበለኝ
ይበለኝ ይበለኝ ይበለኝ ይበለኝ
ይበለኝ ይበለኝ ይበለኝ ይበለኝ

From the album: Misikir