Yeamangu Quine

Yeamangu Quine a song by Rophnan on Foxsoundi — Free Music, Smart Streaming for Everyone

Yeamangu Quine by Rophnan

Yeamangu Quine Lyrics

[00:09.58] አማኝ ተስፋን ከፈጠረው አገኘ
[00:12.87] ተስፋን ይዞ አማኝ ቅኔን ተቀኘ
[00:15.62] ቅኔን ዘርፎ አማኙ ስሙ ናኘ
[00:18.23] ሮፍናን በአምላክ ብቻ ተዳኘ
[00:20.82] እያመነ ሌቱን ሰጥቶ እያደረ
[00:23.31] በይቅርታው ዙሪያው በቸር ታጠረ
[00:25.89] ያጠፋል ግን እንደ አባቱ ዋለ
[00:28.21] ሮፍ- ናን!
[00:29.83] የአማኝ ሴት ቅኔ
[00:31.37] ይመጣሉ!
[00:33.65] አንድ ሁለት አንድ ሁለት
[00:35.22] ውሸት ግን መሳይ እውነት
[00:36.62] ይሄዳሉ!
[00:38.48] ለብሰው ሰናይ ጥለት
[00:40.60] ታማኝ መሳይ ክህደት
[00:41.70] መሽቶ እስኪነጋ-!
[00:44.03] መስሎ የተጠጋ
[00:45.46] ክፍት የተዘጋ
[00:46.76] ላላወቀው-!
[00:48.49] ያዝ በለው ያዝ ያዝ
[00:50.52] ያዝ ያዝ ያዝ አንተ!!!
[00:51.88] ያዝ ከታመቀው (ያዝ!)
[00:53.48] ጥበብ ከሰበቀው (ያዝ!)
[00:54.76] እውነትን ካወቀው ጠበል እርሱ ካፈለቀው (ያዝ!)
[00:57.03] ሦስቱን ዓይን አሻግሮ ከራስ ከታረቀው (ያዝ!)
[00:59.43] በጥቁር ገላ ጥቁር ክር "ቶ" መስቀል አጥልቀው ከእርሱ እንዳትርቅ!!!
[01:02.14] የእናና ግንባር ያወራል
[01:03.77] "ቶ" መስቀል ከፀሐይ ያበራል
[01:04.95] የግንባሯን ኩል ንቅሳት ምክንያቱን ላወቀው (ያዝ!)
[01:06.90] ያዝ በለው ያን የሰው ጥሬ (ያዝ!)
[01:09.79] በል ፍታ የአማኙን ቅኔ
[01:11.94] ከላይ ቃል ከላይ ምት
[01:13.57] ከላይ ጣል ከላይ ስንት
[01:14.71] ከላይ ሰጠኝ ከላይ ስንቅ
[01:15.77] ከላይ ጥበብ ከላይ ጥንት
[01:17.18] ከላይ ካለው የላይ ድንቅ
[01:18.51] በላይ ኃይሉ የላይ ጥግ
[01:19.67] ሰው ከእርሱ እንዳትርቅ!!!
[01:22.60] ባመነው
[01:23.95] ሰው በእምነቱ ልክ ሊያገኝ ግድ ነው
[01:26.34] የታመነ ድንጋይ ዋጋው ወርቅ ነው
[01:28.95] የእጁ አይደለም የእምነት ፍልፍል ነው
[01:31.37] ቤ‐ተ‐ስ‐ኪ‐ያ‐ኑ‐ን ላየው!
[01:33.27] የአማኙ ቅኔ
[01:34.44] አንድ አማኝ ያለው ብርሃን
[01:36.27] ለሺህ ትውልድ ይበራል
[01:38.27] የአማኙ ቅኔ
[01:39.68] ዘመን 'ማይጥለው ጥበብ
[01:41.43] ነገን አልፎ ሊነበብ
[01:43.13] የአማኙ ቅኔ
[01:44.78] የአማኙ ሰው ቅኔ
[01:46.66] ደርሷል ለዘመኔ
[01:48.52] የአማኙ ቅኔ
[01:50.17] ዘመን 'ማይጥለው ጥበብ
[01:51.72] ነገን አልፎ ሊነበብ
[01:53.76] የአማኙ ቅኔ ከፍ
[01:55.70] ማን ብሎ ጠራው ስሜን?
[01:57.57] ሮፍ‐ናን
[01:59.33] አውቋል ልቤ
[02:00.16] ብሎ ከፍታ ላይ ነቅቷል ሳልሣዊ ዓይኔ III
[02:03.36] አመስጋኝ ነኝ ለእነርሱ
[02:05.21] ብራና ፍቀው የእውቀትን ብርሃን ላነሱ
[02:07.89] ብርሃን ለራቀው ሰው ቆመው ጾመው ለከሱ
[02:10.33] ድንጋይ እንደ ቅቤ ቆርጠው ቤቱን ላነፁ
[02:12.92] ድንጋይ የሆነን ልብ መክረው ዘክረው የመለሱ
[02:15.57] "ቶ"
[02:16.12] ይላል የመቋሚያው ላይ አናት "ቆ"
[02:18.53] ሳብዕ ቀስተደመና ቀለማት "ቆ"
[02:21.04] ቤዛ ሚስጥረ ፊደል እናት "ቶ"
[02:23.63] "ቆ" ሮ- ፍናን!
[02:25.80] ገረዓልታን አስተዋለ ፅናቱስ ከየት ነው አለ
[02:28.29] ገረዓልታን የፈለፈሉ እጆች በማይሻር ጥበብ የተካነ
[02:30.89] ገረዓልታን የሚወጡ እግሮች እንደሰው አይደክሙም እርሱ እስካለ
[02:33.47] እምነቱን በእርሱ የጣለ የማይቻለውን ሆነ
[02:35.96] ሆነ!
[02:36.83] እምነት ይዞ በምድር ጉዞ ቀንና ለሊቱን ጣረ
[02:39.14] ከማይታፈስ ከማይደረስ ከሚመስለው ጫፍ ላይ ዋለ
[02:41.84] ፅናትን እምነትን ችሎ መገኘትን ከአማኙ ቅኔ ተማረ
[02:44.12] አመነ! ልቡ ተካበ! ገረዓልታ ሆነ!
[02:46.27] አቦይ ቀሺ!
[02:47.68] ጎይታ ምህረይ!
[02:49.00] የአንተ ፅናት ከዘመን ዘመን እያስተማረኝ
[02:51.14] የአንተ ኪነት ከላይ የመጣው ተስፋ እየሆነኝ
[02:53.20] ሰው አደረገኝ
[02:54.87] ከሰው ደመረኝ
[02:56.26] ጧፍም በጧፍ ይበራል
[02:58.17] ሰውም ሰው አይቶ ይፀናል
[03:02.07] የአንድ አማኝ ጸሎት ሃገር ያክማል
[03:05.93] የአማኙ ቅኔ
[03:07.30] አንድ አማኝ ያለው ብርሃን
[03:09.23] ለሺህ ትውልድ ይበራል
[03:11.10] የአማኙ ቅኔ
[03:12.62] ዘመን 'ማይጥለው ጥበብ
[03:14.43] ነገን አልፎ ሊነበብ
[03:16.34] የአማኙ ቅኔ
[03:17.74] የአማኙ ሰው ቅኔ
[03:19.51] ደርሷል ለዘመኔ
[03:21.46] የአማኙ ቅኔ
[03:22.78] ዘመን 'ማይጥለው ጥበብ
[03:24.66] ነገን አልፎ ሊነበብ
[03:26.79] የአማኙ ቅኔ-!
[03:29.36]
[03:36.57] የአማኙ ቅኔ!
[03:41.45] የአማኙ ቅኔ!
[03:42.18]

From the album: Sidist (VI)