Hagere Nat Habte
Hagere Nat Habte a song by Neway Debebe on Foxsoundi — Free Music, Smart Streaming for Everyone
Hagere Nat Habte Lyrics
የዜማ የቃኔ የቀሳውት ሀገር
የቅዱስ ገዳማት የታቦታት ደብር
ፋሲለደስ አክሱም የታሪክ ምስክር
መስቀል ፅላታችን የእምነታችን ሚስጥር
ገዳማት መስጊዱ ሀውልታችን ሳይቀር
ሀገሬ ሰው ኧረ እንዴት ነው ሀገሬ አፈሩ ኧረ እንዴት ነው
ሀገሬ ወንዙ ኧረ እንዴት ነው ወፉ አራዊቱ ኧረ እንዴት ነው
ባለዝና ያደረገኝ ያ ሸንተረር ያስከበረኝ
ሜዳ ወንዙ የሚያኮራኝ ኧረ እንዴት ነው ዋ! ናፈቀኝ
ያ ወገኔ ያሳደገኝ ያስተማረ ሰው ያረገኝ
ያልከፈልኩት የቀረብኝ ለውለታው ባለዳ ነኝ
ሀገሬን አልረሳም ሀገሬን
ወገኔን አልረሳም ወገኔን
ክብሬና ስሜን
ወጌ ማዕረጌን
ነፃነት ድሌን
እምነት ማተቤን
ሆኦኦኦኦኦኦኦሆሆሆሆይ
የዜማ የቅኔ የቀሳውስት ሀገር
የቅዱስ ገዳማት የታቦታት ደብር
ፋሲለደስ አክሱም የታሪክ ምስክር
መስቀል ፅላታችን የእምነታችን ሚስጥር
ገዳማት መስጊዱ ሀውልታችን ሳይቀር
ሀገሬ ሰው ኧረ እንዴት ነው ሀገሬ አፈሩ ኧረ እንዴት ነው
ሀገሬ ወንዙ ኧረ እንዴት ነው ወፉ አራዊቱ ኧረ እንዴት ነው
የሀይማኖት የታሪክ ሀብታም ወገን ይዤን እኔ አልረታም
የሰው ሀገር አንገት ቢያስደፋም ኩራት ክብሬ ከልቤ አልጠፋም
የናት ያባት ታሪክ ብስራቴ የህት ወንድም የልብ ኩራቴ
ኢትዮጺያዊው ወገኔ ሀብቴ ጋሻ ክንዴ ድጋፍ ጉልበቴ
እናቴን አልረሳም አባቴን
እህቴን አልረሳም ወንድሜን
ስጋና ደሜን
የክፉ ቀኔን
ሚስጥሬ አንጀቴን
የራብ ጥማቴን
በልቶ መጥገብ በሀገር ነበር ለብሶ ማጌጥ በሀገር ነበር
መኩራራትም በወገን ነበር መመካትም በወገን ነበር
ባይል እንጂ እድል ቢከፋ ከገበታስ ማዕድ መች ጠፋ
የራስ ንቆ የሰው መመኘት ባመል ወዶ ወድቆ መገኘት
ሀገሬን አልረሳም ሀገሬን
ወገኔን አልረሳም ወገኔን
ክብሬና ስሜን
ወጌ ማዕረጌን
ነፃነት ድሌን
እምነት ማተቤን
ሁሁሁሁሁሁሁሁሀአሀሁሁ
እምዬ እናቴን እማማ ሀገሬን እምዬ ኢትዮጺያ
የቅዱስ ገዳማት የታቦታት ደብር
ፋሲለደስ አክሱም የታሪክ ምስክር
መስቀል ፅላታችን የእምነታችን ሚስጥር
ገዳማት መስጊዱ ሀውልታችን ሳይቀር
ሀገሬ ሰው ኧረ እንዴት ነው ሀገሬ አፈሩ ኧረ እንዴት ነው
ሀገሬ ወንዙ ኧረ እንዴት ነው ወፉ አራዊቱ ኧረ እንዴት ነው
ባለዝና ያደረገኝ ያ ሸንተረር ያስከበረኝ
ሜዳ ወንዙ የሚያኮራኝ ኧረ እንዴት ነው ዋ! ናፈቀኝ
ያ ወገኔ ያሳደገኝ ያስተማረ ሰው ያረገኝ
ያልከፈልኩት የቀረብኝ ለውለታው ባለዳ ነኝ
ሀገሬን አልረሳም ሀገሬን
ወገኔን አልረሳም ወገኔን
ክብሬና ስሜን
ወጌ ማዕረጌን
ነፃነት ድሌን
እምነት ማተቤን
ሆኦኦኦኦኦኦኦሆሆሆሆይ
የዜማ የቅኔ የቀሳውስት ሀገር
የቅዱስ ገዳማት የታቦታት ደብር
ፋሲለደስ አክሱም የታሪክ ምስክር
መስቀል ፅላታችን የእምነታችን ሚስጥር
ገዳማት መስጊዱ ሀውልታችን ሳይቀር
ሀገሬ ሰው ኧረ እንዴት ነው ሀገሬ አፈሩ ኧረ እንዴት ነው
ሀገሬ ወንዙ ኧረ እንዴት ነው ወፉ አራዊቱ ኧረ እንዴት ነው
የሀይማኖት የታሪክ ሀብታም ወገን ይዤን እኔ አልረታም
የሰው ሀገር አንገት ቢያስደፋም ኩራት ክብሬ ከልቤ አልጠፋም
የናት ያባት ታሪክ ብስራቴ የህት ወንድም የልብ ኩራቴ
ኢትዮጺያዊው ወገኔ ሀብቴ ጋሻ ክንዴ ድጋፍ ጉልበቴ
እናቴን አልረሳም አባቴን
እህቴን አልረሳም ወንድሜን
ስጋና ደሜን
የክፉ ቀኔን
ሚስጥሬ አንጀቴን
የራብ ጥማቴን
በልቶ መጥገብ በሀገር ነበር ለብሶ ማጌጥ በሀገር ነበር
መኩራራትም በወገን ነበር መመካትም በወገን ነበር
ባይል እንጂ እድል ቢከፋ ከገበታስ ማዕድ መች ጠፋ
የራስ ንቆ የሰው መመኘት ባመል ወዶ ወድቆ መገኘት
ሀገሬን አልረሳም ሀገሬን
ወገኔን አልረሳም ወገኔን
ክብሬና ስሜን
ወጌ ማዕረጌን
ነፃነት ድሌን
እምነት ማተቤን
ሁሁሁሁሁሁሁሁሀአሀሁሁ
እምዬ እናቴን እማማ ሀገሬን እምዬ ኢትዮጺያ
From the album: Best of Neway Debebe Collection
-
Maebel New by Neway Debebe , -
Teteyeki Was by Neway Debebe , -
Hagere Nat Habte by Neway Debebe , -
Ye Ayne Abeba Nesh by Neway Debebe , -
Yetikimt Abeba by Neway Debebe , -
Lalkedash Kal Alebign by Neway Debebe , -
Yelefku Ende Hon Banchi Sefer by Neway Debebe , -
Siwodush Eweki by Neway Debebe , -
Egnaw Enitarek by Neway Debebe , -
Ye-Fikir Emebet by Neway Debebe , -
Yegna Loga by Neway Debebe , -
Wuletash Alebign by Neway Debebe , -
Ayaya by Neway Debebe , -
Afar Gemalitua by Neway Debebe , -
Yefikir Gedam by Neway Debebe ,